ስለኔ የሴቶች አቅም ግንባታና የበጎ አድራጎት ድርጅት ከኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስርያ ቤት አስተባባሪነት በክብረት ዶ/ር ኤርጌጎ ተስፋዬ የተመራ ልኡክ ጋር በጋራ በመሆን በሽሮ ሜዳ በሚገኘው በምስካበ የአረጋውያንና ህፃናት መርጃ ማህበር በመገኘት ጉብኝት አድርገናል ።በጉብኝታችን ድርጅታችን ስለኔ የማህበሩ ስራ ለማገዝ የ50,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገናል። ስለኔ የሴቶች አቅም ግንባታና የበጎ አድራጎት ድርጅት በል/ክ/ከ/ወ/4 ለሚገኙ ለ100 ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችን የፋሲካ በአል የአስቤዛ ድጋፍ አድርገናል።